የታጋዮች ህብረት
ለሃገር ለወገን
ድረሱልኝ ጥሪ አለኝታ በመሆን
መፍትሄ አፍልቆ ታግሎ ለማታገል
ጥጥሩ ይላላ የላላው ይጠጥር
እኛው ተባብለን ከኛው ለኛው ይቅር
ገበናን ሸፍነን የቤታችን ሚስጥር
ባንድነት በፍቅር በመቻቻል መንፈስ
ትግላችን ይታደስ
መረቡ ይዘርጋ ገመዱ ይገመድ
በኢትዮጵያዊነት ባገር እንዛመድ
በሃሜት በወሬ ተጠላልፈን እንዳንወድቅ
የቁርኝታችን ሰንሰለቱ ይጥበቅ
በተናጠል ጉዞ መንገዱ አይርዘም
ክፍተቱን እናጥብብ -ስንጥቁን እንድፈን
ስንሮጥ እንዳሻን -ጊዜያችን አይባክን
ታጋዮች በህብረት ክንዳችን ይፈርጥም
ስልታችን ይቀናጅ አቅጣጫን ይጠቁም
አዲስ
ግንቦት 25 2007