የኢ.ማ.ኖ. 2008 ፕሮጀክቶች ዝርዝር፤

የሚከተሉት ፕሮጀክቶች የተነደፉት 2008 ውስጥ እንዲጠናቀቁ ነው፡፡ ፕሮጀክቶቹ እንዴት እንደሚጠናቀቁ ኮሚቴው እቅድና የስራ ድርሻ ካከፋፈለ በኋላ ለተግባራዊ እንቅስቃሴ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡
ኢትዮጵያውያንም ተካፋይ እንደሚሆኑ ማህበሩ በኢትዮጵያውያን ላይ ይተማመናል፡፡

የፕሮጀክት ስም የፕሮጀክቱ አላማ
የኢትዮጵያ ቀን 2008 ኢማኖ 10 ዓመት ስለሚሞላው ቀኑ ይከበራል፡፡ ስለ ማህበሩ ታሪክ ባጭሩ፣ እንቅስቃሴወችና ሂደት ገለጻ ይደረጋል፣ ሙዚቃ፣ ዳንስ፣ አውደ ትዕይንት፣ ፈሊጥ፣ የተለያዩ ምግቦች ወዘተ ይኖራል፡፡ ቦታው ኦስሎ ሶፊየንበርግ ፓርክ ነው፡፡ ቅዳሜ ነሃሴ 16 ከ1200 - 2000. ዝግጅቱ ለሁሉም ክፍት ነው፡፡
የኢትዮጵያውያን የበጋ ስፖርት ፊስቲቫል ፌስቲቫሉ የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የጠረጴዛ ኳስና የሩጫ ውድድር ይገኝበታል፡፡
የትምህርት እርዳታ ለታዳጊ ወጣቶችና ለወጣቶች በሳምንት ከ1-2 ጊዜ የትምህርት እርዳታ መስጠት፡፡
የባህልና ያብሮ መዋሀድ ጉባኤ ቤተሰብና አብሮ መኖርን በተመለከተ እውቀትን ማስፋትና ማሳደግ፡፡
የባህልና ባህሪ ለውጥ ኖርዌይ ውስጥ ለመኖር ቀለል እንዲል አስተሳሰብና ባህሪን በተመለከተ ጉባኤ ማድረግ፡፡
ስነ ጥበብና ውህደት ኢትዮጵያውያን ስነ ጥበበኞች በኖርዌጅኛ እንዲጽፉ ማበረታታት፡፡