Etiopisk Forening i Norge

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይና በዓላት

ኢማኖ አድስ ዓመት፣ ገና በዓል እና ፋሲካን ከኢትዮጵያውያን ጋር ያከብራል፡፡ ኢድ አልፈጥርና የመሳሰሉትንም ወደፊት ለማክበር ማህበሩ ኢትዮጵያውያንን ያበረታታል፡፡ እነዚህ በዓላትን ስናከብር ልክ እንደ ኢትዮጵያ ውስጥ በዕለቱ ቀን ባይሆንም ቀራቢው ቅዳሜ ላይ እናከብራለን፡፡ በርግጥ ግለሰቦችና የሀይማኖት ተቋማት በዕለቱ ላይ እንደሚያከብሩ አይዘነጋም፡፡

ነዚህ ሦስት በዓላት ዝግጅቶች ማህበሩ ቅድሚያ እንዳለው በሰፊው የታወቀ ነው፡፡ ለአመታት ሲሰራበትም ቆይቷል፡፡ ከማህበሩ ውጭ ሰፊ ዝግጅት የሚያደርጉ ክፍሎች ቀደም ብለው ማህበሩን ቢያሳውቁት ጥሩ ነው፡፡ ድርብ ዝግጅቶች እንዳይኖሩ ማህበሩ ከሌሎች ክፍሎች ጋር በጋራ መፍትሄ ለማግኘት ይጥራል፡፡
ዳሜ ሊመረጥ የቻለበት ምክንያት ውጭ ስለምኖርና ከስራም ሆነ ከትምህርት ነጻ የምንሆንበት ቀን ቅዳሜ ስለሆነ ነው፡፡


ነዚህ በዓላት በሰፊውና ባዝናኝ መልኩ እንዲከበሩ ማህበሩ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ ቀን ላይ የልጆችና የቤተሰቦች ዝግጅቶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ እንቅስቃሴዎችም የልጆች ጨዋታ፣ ውድድር፣ ሽልማት፣ የልጆች ዘፈን፣ ምግብና መጠጦች፣ የቡና ስናስርዕት የመሳሰሉት ይዘጋጃሉ፡፡


ሽት ላይ ደግሞ ከምግብና ከመጠጥ ጋር የሙዚቃ ምሽት አለ፡፡ ለወደፊቱ በቀኑና በምሽቱ መርሃግብሮች መካከል በሰፊ ሰሌዳ ፊልም ለማሳየት ማህበሩ እቅድ አለው፡፡