|
|||
Choose language
|
ስለዚህ ማንኛውም ዜጋ አገሩ ውስጥም ሆነ ሌላ አገር ቢኖርም፤ እዚህ ጽሁፍ ላይ የተጠቀሰውን የሥራ አፈላለግ ደንብና ስርአት ቢያውቅ እጅግ ይጠቅመዋል፡፡ ይህንን ስልት በተገቢው ከተጠቀሙበት ከአንድ ስራ በላይም ሊያገኙ ስልሚችሉ ስራ መምረጥ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ እኔ ባንድ ወቅት ላይ ሁለት ሥራዎች አግኝቼ አንዱን የተሻለውን ልመርጥ ችያለሁ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ሥራ ላይ እያለሁ ቢሆንም ሶስት ዓመታት ሙሉ የተሻለ ሥራ ፍለጋ ላይ ስለነበርኩ በራሴ ስህተትና ትምህርት ከወሰድኩ በኋላ ነው፡፡ የመጀመሪያም ሆነ የተሻለ ሥራ ለማግኘት ቋሚ የሆነ ህግና ደንብ የለም፡፡ እንደ ሁኔታው ይለያያል፡፡ በግሌ የማውቀውንና የወሰድኩትን ልምድ ለሌሎች ባካፍል ግን በጣም ደስ ይለኛል፡፡ እዚህ የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ መረበ ገጽ ላይ የቀረቡት የስራ አፈላለግ ስልቶች በደንብ ተነበው በተገቢው ከተፈፀሙ አንድ ስራ ማግኘት ቀርቶ ስራ ለመምረጥም ጭምር እድል ያሰፋሉ፡፡ ስልቶቹ የተጻፉት ባንድ ንጋት ምርምር አይደለም፡፡ ስለዚህ እርስዎ ውጤት ለማግኘት ከፈለጉ በስልቶቹ መሰረት ልምምድ፣ ክትትልና ትኩረት ማድረግ አለብዎት፡፡ በነዚያ ሦስት አመታት ውስጥ ከመቶ በላይ ማመልከቻዎች ልኬ ወደ በርካታ ቃለ ምልልሶች ተጠርቼ ነበር፡፡ በደንብ እየታሸሁኝና እየበሸኩኝ ስህተትም ሆነ ትምህርት ወስጃለሁ፡፡ ስለዚህ እርስዎ ስልቱን በተገቢው ካዎቁት ልክ እንደኔ ማንም ወገኛ ስራ ቀጥሪ በነገር አያሸዎትም!!! አሁን ኮተት አታብዛብኝ፥ ይልቅስ ወደ ቁም ነገሩ እንግባ አይሉኝም አንዴ…? በቃ እሺ… ያገሩን ባህልና ቋንቋ ከሞላ ጎደል መቻል፣ የህዝቡን ያኗኗርና የአቀራረብ ዘይቤንም በቅጡ ማወቅ ደህና ስራ ለማግኘት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ይህንን ማዎቅ ስራ ከማግኘትም ባሻገር በግል ህይወታችንና በሌሎች የማህበራዊ ጉዳዮች ላይም ጭምር በዕውቀት እንዲንዳብር ይረዳናል፡፡
|
- | |
|
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ሁሉም መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ www.ethionorway.org e-mail: ethionor@broadpark.no | |||