የኢ.ማ.ኖ. 2007 ፕሮጀክቶች ዝርዝር፤
የሚከተሉት ፕሮጀክቶች ለ2007 የተነደፉና በ2007 ውስጥ የሚጠናቀቁ ናቸው፡፡ ፕሮጀክቶቹ እንዴት እንደሚጠናቀቁ ኮሚቴው አሁን እቅድ እያወጣ ነው፡፡ እቅዱ ሲያልቅ ለተግባራዊ እንቅስቃሴወች ማስታወቂያ እናወጣለን፡፡ ኢትዮጵያውያንም ተካፋይ እንደሚሆኑ ማህበሩ በኢትዮጵያውያን ላይ ይተማመናል፡፡
| የትምህርት እርዳታ |
ለታዳጊ ወጣቶችና ለወጣቶች በሳምንት ከ1-2 ጊዜ የትምህርት እርዳታ መስጠት፡፡ |
| ስፖርት |
መጪው በጋ ላይ የግር፣ የመረብና የጠረንጴዛ ኳስ እና የሩጫ ውድድር ኦስሎ ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ይደረጋል፡፡ |
| የባህልና የውህደት ጉባዔ |
ባህልንና ኖርዌይ ውስጥ መዋሀድን በተመለከተ ጉባዔዎች ይካሄዳሉ፡፡ |
| ጉባዔ ስለግረዛ |
ግረዛ የሚያስከትለውን አጸፋ በተመለከተ ጉባዔዎች ይደረጋሉ፡፡ |
| ደንብና ህግ ኖርዌይ ውስጥ |
የኖርዌይ ደንብና ህግን ለአዲስ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች የበለጠ እንዲያውቁ ማድረግ፡፡ |
| የሴቶች አቅምን ግንባታ |
የኖርዌይ ህግ ስለ ልጅ፣ ቤተሰብና ትዳር እንዲሁም ዘመናዊ ልጅ አስተዳደግ፡፡ |
| የዕውቀት ፕሮጀክት 2007 |
ክለባችን ውስጥ ቢያንስ ሦስት አስሊዎች ይኖሩናል፡፡ የአስሊ መሰረታዊ ትምህርት መስጫ፣ የስራ ፍለጋ ማስተማሪያ፣ የትርጉም ስራዎች መስሪያ፣ ለወጣቶች የቤት ስራ መርጃ ወዘተ ይውላሉ፡፡
ማተሚያ፣ ፋክስ ማድረጊያና ማሰሻ ይኖረናል፡፡
|