Etiopisk Forening i Norge
በአማርኛ ለመጻፍ አስፈላጊ ቁሳቁሶች....

ይህ መመሪያ የሚሰራው ዊንዶውስ ኤክስፒና ዊንዶውስ 2000 ላይ ነው።

አማርኛ አስሊ ላይ መጻፍ ቀላል ነው፡፡ መጀመሪያ ግን አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ማግኘትና አስሊውን በአማርኛ እንዲሰራ ዝግጁ ማድረግ አለብዎት፡፡ ሦስት ነገሮች ያስፈልጉዎታል፡፡
   keyman ( የተለያዩ ቋንቋዎችን ዋና ነጂ ወይም ተቀባይ ነው፡፡ )
   amh-uni ( ኪማን አማርኛ ቋንቋ እንዲያውቅ ነጋሪ ወይም አቀባይ ነው፡፡)
   Amharic Font ( አማርኛ ፊደል ነው፡፡)

 ስቱም አስፈላጊ ነገሮች በነጻ ስለሆኑ ፈገግ ይበሉ፡፡ ኪማን ለግለዎ እቤትዎ ውስጥ መጠቀሚያ እንጂ ለንግድ አይደለም፡፡ ስለኪማን የበለጠ ለማወቅ http://www.tavultesoft.com/ ይጎብኙ፡፡ ሦስቱም ተቀናጅተው በደንብ እንዴት በአማርኛ መጻፍ እንደሚያስችሉ በቅድመ-ተከተል እነግርዎታለሁ፡፡ ቅደመ-ተከተሉን ግን በትክክል ይከተሉ!!!
ጀመሪያ ስለ keyman, amh-uni እና Amharic Font ፀባይና የስራ ድርሻ ባጭሩ እናያለን፡፡
keyman የተለያዩ ቋንቋዎችን እንዲያውቅ ተደርጎ የተሰራ ፕሮግራም ነው፡፡ ለምሳሌ በህንድኛ፣ በአማርኛ፣ በግሪክኛ፣ በአርብኛ ወዘተ እንዲሰራ ተደርጎ ተሰርቷል፡፡ keyman ግን እርስዎ በምን አይነት ቋንቋ መግባባት እንደሚፈልጉ ማወቅ አለበት፡፡ ስለዚህ amh-uni የሚያስፈልገው ይህ የአማርኛ ቋንቋ ነው ብሎ ለኪማን ለመንገር ነው፡፡ Amharic Font የሚያስፈልገው ደግሞ ተጠቃሚው በአማርኛ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብ የአማርኛ ፊዴላት ስለሚያስፈልጉ ነው፡፡


ጭሩ አባባል፤ keyman የተለያዩ አገሮችን ቋንቋዎች የሚችል አንድ ብልጣ ብልጥ ሰው ነው እንበል፡፡ ይህ ብልጥ ሰውዬ ግን በሆነ ቋንቋ ካላናገሩት በስተቀር ዝም ይላል፡፡ ተፈጥሮውም እንደዚሁ ነው፡፡ ስለዚህ እርስዎ አቶ ብልጡ ኪማንን፤ እኔ አማርኛ እችላለሁ ብለው amh-uniንና Amharic Fontን ለኪማን በመስጠት እራስዎን ከኪማን ጋር ማስተዋወቅ አለብዎት፡፡

ከዚህ ብልጥ ሰውዬ ጋር በሚያውቁት በአማርኛ ቋንቋ ለመግባባት ምን ማድረግ እንዳለብዎት የሚቀጥሉትን መመሪያዎች ይከተሉ፡፡

ኪማንን ያዘጋጁ፡፡



-