Etiopisk Forening i Norge

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ባጭሩ፤

ትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ በግለሰቦች አነሳሽነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1987 ጀምሮ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ከ1998 ጀምሮ ግን በኖርዌይ ውስጥ እንደ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቦና እውቅና አግኝቶ ይንቀሳቀሳል፡፡ ማህበሩ በየሁለት አመቱ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ተወካዮች ይመርጣል፡፡ እንዚህም ተወካዮች ለሁለት አመታት ያክል ማህበሩን ይመራሉ፡፡ የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ሰላምንና ዴሞክራሲን ለሚሹ ሁሉንም ኢትዮጵያውያንንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለማስተናገድ ምንጊዜም ክፍት ነው፡፡ ወደፊትም በዚሁ መልክ ይቀጥላል፡፡ ማህበራችን ማንንም በዘር ወይም በሃይማኖት አይለይም፡፡ ስለዚህ ኢ.ማ.ኖ. የሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ለማሟላት የግለሰብ ነጻነትን ያስቀድማል፡፡
ኢ.ማ.ኖ. ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን እንድሁም ስለኖርዌይና ኖርዌጅያውያን ቀና አስተሳሰብና ግንዛቤ አለው፡፡ ማህበሩ በኖርዌይ ውስጥ ተሰሚነት ኖሮት ተጽዕኖ እንዲያደርግ ኢትዮጵያውያን በሰፊው የማህበሩ ተሳታፊና አባል እንደሚሆኑ ማህበሩ በኢትዮጵያውያን ላይ ይተማመናል፡፡


ማህበሩ አንደኛውና ዋናው አላማ በኢትዮጵያውያን መካከል ስምምነትና ውህደትን የበለጠ ለማዳበር ነው፡፡ ከዚህም በማያያዝ የተለያዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴወችና ውይይቶች ለማድረግ እቅድ አለው፡፡ ለምሳሌ፤ የኖርዌይን ባህልና ወግ እንልመድ፣ የራሳችንንም አንርሳ፣ ስለ ነጻነትን አሳልፎ መስጠትና የሚያመጣው ጣጣ፣ ስለ ሙያና ስራ ማግኘት፣ ስለ ቀጠሮና ምንነት በመሳሰሉት ላይ ትምህርታዊ ውይይት ለማድረግ እቅድ አለው፡፡

ህበራችንም እንዲሻሻል አንዳንድ ምቹና ምክንያታዊ ለውጦች እናደርጋለን፡፡ አዝናኝና ትምህርታዊ ምሽቶችም ይኖሩናል፡፡ ይህንን በተመለከተ ማስታወቂያዎችን ቀደም ብለን እንለጥፋለን፡፡ እነዚህንም አላማዎች ለማሳካት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሁሉ እንደሚተባበሩን እንተማመናለን፡፡